ዘኍል 31:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እንግዲህ ወንዱን ሁሉ በአለበት ግደሉ፥ ወንድንም የምታውቀውን ሴት ሁሉ ግደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ወንዶቹን ልጆች ሁሉ፣ ወንድ ያወቁትንም ሴቶች በሙሉ ግደሏቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፥ ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አሁን እያንዳንዱን ወንድ ልጅና እያንዳንዲቱን ከወንድ ጋር የተገናኘች ሴት ግደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ ከልጆቹ ወንዱን ሁሉ ግደሉ፥ ወንድንም በመኝታ የሚያውቁትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ። |
አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጣት ጊዜ፥ በእርስዋ ያሉትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ስለት ትገድላቸዋለህ፤
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
ማኅበሩም ወደዚያ ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላን ሰዎችን ልከው፥ “ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ሴቶችንም ሕዝቡንም በሰይፍ ስለት ግደሉ።