Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ማኅ​በ​ሩም ወደ​ዚያ ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን ልከው፥ “ሂዱ በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድም ያሉ​ትን ሰዎች ሴቶ​ች​ንም ሕዝ​ቡ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ግደሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ስለዚህ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ተዋጊዎች ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ሄደው በዚያ የሚኖሩትን በሙሉ ሴቶቹንና ሕፃናቱን ጭምር በሰይፍ እንዲፈጇቸው ጉባኤው መመሪያ ሰጥቶ ላካቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ስለዚህ ዐሥራ ሁለት ሺህ ተዋጊዎች ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሄደው በእዚያ የሚኖሩትን በሙሉ ሴቶቹንና ሕፃናቱን ጭምር በሰይፍ እንዲፈጇቸው ጉባኤው መመሪያ ሰጥቶ ላካቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህ ጉባኤው “ወደ ያቤሽ ሄዳችሁ ሴቶችና ሕፃናት ሳይቀሩ የገለዓድ ኗሪዎችን በሰይፍ ስለት ግደሉ!” ብለው ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላንን ላኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ማኅበሩም ወደዚያ አሥራ ሁለት ሺህ ኃያላን ሰዎች ሰድደው፦ ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ከሴቶችና ከሕፃናት ጋር በሰይፍ ስለት ግደሉ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 21:10
9 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ወን​ዱን ሁሉ በአ​ለ​በት ግደሉ፥ ወን​ድ​ንም የም​ታ​ው​ቀ​ውን ሴት ሁሉ ግደሉ።


የዚ​ያ​ችን ሀገር ሰዎች በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ ትመ​ታ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ሀገ​ሪ​ቱን፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ትረ​ግ​ማ​ለህ።


ኢያ​ሱም የዛ​ራን ልጅ አካ​ንን፥ ብሩ​ንም፥ ልብ​ሱ​ንም፥ ልሳነ ወር​ቁ​ንም ወደ አኮር ሸለቆ ወሰ​ዳ​ቸው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም፥ በሬ​ዎ​ቹ​ንም፥ አህ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ በጎ​ቹ​ንም፥ ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ ንብ​ረ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ ዔሜ​ቃ​ኮር ወሰደ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ስላ​ል​ወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበ​ርና፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ።


እነ​ር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ። እነ​ሆም፥ ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባ​ኤው ማንም አል​ወ​ጣም ነበር።


ሕዝ​ቡም በተ​ቈ​ጠሩ ጊዜ፥ እነሆ፥ ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ነዋ​ሪ​ዎች ሰው አል​ተ​ገ​ኘም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ አለ፥ “ሜሮ​ዝን ርገሙ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በኀ​ያ​ላን መካ​ከል ወደ እርሱ ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በቤ​ቶ​ችዋ ያሉ​ትን ሰዎች ፈጽ​ማ​ችሁ ርገሙ።”


ጥም​ዱ​ንም በሬ​ዎች ወስዶ በየ​ብ​ል​ታ​ቸው ቈራ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ዳርቻ ሁሉ በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እጅ ላከና፥ “ሳኦ​ል​ንና ሳሙ​ኤ​ልን ተከ​ትሎ የማ​ይ​ወጣ ሁሉ፥ በበ​ሬ​ዎቹ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል” አለ። ድን​ጋ​ጤም በሕ​ዝቡ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደቀ፤ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ጮኹ።


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos