የይስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይህ ነው፤ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው።
ዘኍል 31:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ፥ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድያማውያኑ የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም በሙሉ አቃጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሞቻቸውንና የሰፈሩበትን ቦታ ሁሉ አቃጠሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። |
የይስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይህ ነው፤ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው።
የግብፅም ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጋዜርን ያዘ፤ በእሳትም አቃጠላት፤ በሜርጎብ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንንም ገደላቸው፤ ለልጁም ለሰሎሞን ሚስት እነዚያን አገሮች ትሎት አድርጎ ሰጥቶአት ነበር።
ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ ባዕዳን ይበሉታል፤ ጠላትም ያጠፋዋል፤ ባድማም ያደርገዋል።
የምድያምንም ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና ዕቃቸውን፥ ንብረታቸውንና ኀይላቸውን በዘበዙ።
ከተማዪቱንም፥ በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፤ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን፥ የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ሴቄላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በአዜብ በሰቄላቅም ላይ ዘምተው ነበር፤ ሴቄላቅንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥