“አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤
ዘኍል 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰማው በኋላ ግን ቢከለክላት ኀጢአቱን ይሸከማል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ነገሮቹ ከሰማ በኋላ እንዲቀሩ ካደረገ ግን ለፈጸመችው በደል በኀላፊነት የሚጠየቀው ራሱ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን ነገሩን ከሰማ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከንቱ ቢያደርገው በደልዋን ይሸከማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ቈየት ብሎ ስእለቱን የሚቃወም ከሆነ ለስእለቱ አለመፈጸም ኀላፊ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማው በኋላ ግን ከንቱ ቢያደርገው ኃጢአትዋን ይሸከማል። |
“አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ስእለቷን ቢከለክላት፥ ስለ ስእለቷ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ ከአፍዋ የወጣው ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከልክሏታል፤ እግዚአብሔርም ያነጻታል።
ነገር ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለቷን ሁሉ፥ በእርስዋም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ ያጸናዋል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል።
እርስዋ በብላቴንነቷ ጊዜ በአባቷ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው ሥርዐት ይህ ነው።
አባቷ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷ፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባቷ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል።
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷና ራስዋን ያሰረችበት መሐላ አይጸኑም፤ ባልዋ ከልክሎአታልና፤ እግዚአብሔርም ይቅር ይላታል።
በዚህም አይሁዳዊ፥ ወይም አረማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ናችሁና።