ዘኍል 30:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለቷን ሁሉ፥ በእርስዋም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ ያጸናዋል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ባሏ ግን ስለ ጕዳዩ ከዕለት ወደ ዕለት ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር ስእለቶቿን ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸውን ነገሮች ሁሉ እያጸናላት ነው ማለት ነው፤ ስለ ነገሮቹ ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት በመቅረቱ አጽንቶላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባልዋ ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለትዋን ሁሉ በእርሷም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ አጽንቶታል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ባልዋ ስለ ጉዳዩ በሰማበት ቀን ማግስት ምንም ተቃውሞ ያላቀረበ ከሆነ ስእለትዋንና በመሐላ የገባችውን ቃል ሁሉ መፈጸም ይኖርባታል፤ ስለ ጉዳዩ በሰማበት ቀን ተቃውሞ አለማቅረቡ ፈቃደኛ መሆኑን ያረጋግጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋ ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለትዋን ሁሉ በእርስዋም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ አጽንቶታል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል። |