ዘኍል 30:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ነገር ግን ባልዋ ስለ ጉዳዩ በሰማበት ቀን ማግስት ምንም ተቃውሞ ያላቀረበ ከሆነ ስእለትዋንና በመሐላ የገባችውን ቃል ሁሉ መፈጸም ይኖርባታል፤ ስለ ጉዳዩ በሰማበት ቀን ተቃውሞ አለማቅረቡ ፈቃደኛ መሆኑን ያረጋግጣል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ይሁን እንጂ ባሏ ግን ስለ ጕዳዩ ከዕለት ወደ ዕለት ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር ስእለቶቿን ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸውን ነገሮች ሁሉ እያጸናላት ነው ማለት ነው፤ ስለ ነገሮቹ ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት በመቅረቱ አጽንቶላታል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ባልዋ ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለትዋን ሁሉ በእርሷም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ አጽንቶታል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ነገር ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለቷን ሁሉ፥ በእርስዋም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ ያጸናዋል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ባልዋ ግን በየዕለቱ ዝም ቢላት፥ ስእለትዋን ሁሉ በእርስዋም ላይ ያለውን መሐላ ሁሉ አጽንቶታል፤ በሰማበት ቀን ዝም ብሎአታልና አጽንቶታል። Ver Capítulo |