የእስራኤል ልጆችም እንደ አዘዛቸው አደረጉ፤ ዮሴፍም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን እንደ ነገረው ሰረገሎችንና ለመንገድ ስንቅን ሰጣቸው፤
ዘኍል 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና አሮንም እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ እግዚአብሔር እንደ አዘዛቸው ቈጠሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል በታዘዘው መሠረት እነዚህን ቈጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንደ ጌታ ቃል፥ እንደ ታዘዘው ቈጠራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም በእግዚአብሔር ቃል እንደታዘዘው ቈጠረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው ቈጠራቸው። |
የእስራኤል ልጆችም እንደ አዘዛቸው አደረጉ፤ ዮሴፍም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን እንደ ነገረው ሰረገሎችንና ለመንገድ ስንቅን ሰጣቸው፤
“የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው።”
በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ ከሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ በየወገናቸው የተቈጠሩት ሁሉ ሃያ ሁለት ሺህ ነበሩ።
የጌድሶን ልጆች አገልግሎት ሁሉ፥ በተራቸውም ሁሉ፥ በሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በስማቸውና በተራቸውም ትቈጥራቸዋለህ።
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠሩአቸው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገለግሉ ዘንድ የሚገቡት ሁሉ፥ የቀዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ የጌድሶን ልጆች ቍጥር ይህ ነው።
እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ እጅ ተቈጠሩ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ።
የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፤ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጕዳትም ሁሉ ይቆማልና፤