La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 28:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሌላ​ው​ንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የመ​ጠ​ጡን ቍር​ባን በማ​ለዳ እን​ዳ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቀ​ር​ቡ​ታ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሁለተኛውንም ጠቦት ጧት ባቀረባችሁት ዐይነት አድርጋችሁ ከእህል ቍርባኑና ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ ማታ አቅርቡት፤ ይህም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባለህ፤ የእህሉን ቁርባንና የመጠጡን ቁርባን በማለዳ እንዳቀረብህ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሲመሽም ሁለተኛውን ጠቦት ልክ የመጀመሪያው በቀረበበት ሁኔታ የመጠጡንም መባ ጨምራችሁ አቅርቡ፤ እርሱም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባለህ፤ የእህሉን ቍርባንና የመጠጡን ቍርባን በማለዳ እንዳቀረብህ በእሳት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ታቀርበዋለህ።

Ver Capítulo



ዘኍል 28:8
6 Referencias Cruzadas  

የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


ከክ​ን​ፎ​ቹም ይሰ​ብ​ረ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ለ​የ​ውም። ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያኖ​ረ​ዋል፤ መሥ​ዋ​ዕቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።


የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ለአ​ንድ ጠቦት የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተ​ኛው እጅ ነው፤ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጠጥ ቍር​ባን መጠጥ ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ።


“በሰ​ን​በ​ትም ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየ​ልን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባ​ና​ቸው ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።