Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 28:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባለህ፤ የእህሉን ቍርባንና የመጠጡን ቍርባን በማለዳ እንዳቀረብህ በእሳት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ታቀርበዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሁለተኛውንም ጠቦት ጧት ባቀረባችሁት ዐይነት አድርጋችሁ ከእህል ቍርባኑና ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ ማታ አቅርቡት፤ ይህም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባለህ፤ የእህሉን ቁርባንና የመጠጡን ቁርባን በማለዳ እንዳቀረብህ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሲመሽም ሁለተኛውን ጠቦት ልክ የመጀመሪያው በቀረበበት ሁኔታ የመጠጡንም መባ ጨምራችሁ አቅርቡ፤ እርሱም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሌላ​ው​ንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የመ​ጠ​ጡን ቍር​ባን በማ​ለዳ እን​ዳ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቀ​ር​ቡ​ታ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 28:8
6 Referencias Cruzadas  

የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል። ካህኑም ሁሉን አቅርቦ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ ነው።


በክንፎቹም ይቀድደዋል፥ ነገር ግን አይከፍለውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥለዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ ነው።


የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን አድርጎ በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።


የመጠጡ ቍርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ነው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለእግዚአብሔር ለመጠጥ ቍርባን መጠጥ ታፈስሳለህ።


በሰንበትም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ለእህልም ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ የመጠጡንም ቍርባን ታቀርባላችሁ።


ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየልን ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባናቸው ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos