ዘኍል 28:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚሁ ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ እስከ ሰባትም ቀን ድረስ ቂጣ ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው ቂጣ ይበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ነው፤ ለሰባት ቀኖች መበላት ያለበት እርሾ ያልነካው ቂጣ ብቻ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። |
የቂጣውን በዓል ጠብቁ፤ በአዲስ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝኋችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።
“የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በሚያዝያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በሚያዝያ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።