በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።
ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።
ከመጠጡ መባና ከሚቀርበው ከዘወትር መሥዋዕት ጋር ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በየሰንበቱ ይቅረብ።
በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ለማጠን፥ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ እኔ ልጁ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራለሁ፤ እርሱንም እቀድሳለሁ።
ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዐታቸው በየቀኑ ሁሉ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየበዓላቱም፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየዳሱም በዓል ቍርባን ያቀርቡ ነበር።
መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን አልወድም።
ማልዶ ከሚቀርበው በዘወትር ከሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ እነዚህን ታቀርባላችሁ።
እንዲህም በላቸው፦ በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።
“በሰንበትም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ለእህልም ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ የመጠጡንም ቍርባን ታቀርባላችሁ።
ለኀጢአት መሥዋዕት፥ ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ። ከሚያስተሰርየው ከኀጢአት መሥዋዕት፥ በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጥ ቍርባናቸውም ሌላ አቅርቡት።
ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።
ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየልን ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባናቸው ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።
ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።
ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።
በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን እንደ ሕጋቸው ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።