እነሆ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እንዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።
ዘኍል 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢአት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእግዚአብሔር ላይ በተሰበሰቡ ወገን መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋራ አልነበረም፤ የሞተው ግን በራሱ ኀጢአት ሲሆን፣ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ቆሬን በመከተል በጌታ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባታችን አንድ እንኳ ወንድ ልጅ ሳይወልድ በምድረ በዳ ሞተ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋር ተባባሪ አልነበረም፤ የሞተውም በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእግዚአብሔር ላይ በተሰበሰቡ ወገን መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም። |
እነሆ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እንዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።
እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፤ በዚያም ይሞታሉ።”
በምስክሩም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር፥ በአለቆቹም፥ በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “እኔ እሄዳለሁ ትሹኛላችሁም፤ ነገር ግን አታገኙኝም፤ በኀጢኣታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበትም እናንተ መምጣት አይቻላችሁም” አላቸው።
ስለዚህም በአንድ ሰው በደል ምክንያት ኀጢአት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለዚችም ኀጢአት ሞት ገባ፤ እንደዚሁም ሁሉ ኀጢአትን ስለ አደረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ።
ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች።