አሮንም የአሚናዳብን ልጅ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ። እርስዋም ናዳብንና አብዩድን፥ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።
ዘኍል 26:61 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሲና በረሃ በእግዚአብሔር ፊት ከሌላ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ናዳብና አብዩድ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ስላቀረቡ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታም ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዳብና አቢሁ ያልተቀደሰ እሳት ለእግዚአብሔር ከማቅረባቸው የተነሣ ተቀሥፈው ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ፊት ሌላ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። |
አሮንም የአሚናዳብን ልጅ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ። እርስዋም ናዳብንና አብዩድን፥ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።
ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በእግዚአብሔር ፊት ከሌላ እሳት ጭረው አምጥተዋልና በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር ከአባታቸው ከአሮን ጋር በክህነት ያገለግሉ ነበር።