ዘኍል 24:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቄጤዎንም እጅ የሚወጣው አሦርንና ዕብራውያንን ያስጨንቃል፤ እነርሱም በአንድነት ይጠፋሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎች ይመጣሉ፤ አሦርንና ዔቦርን ይይዛሉ፤ እነርሱም ደግሞ ይደመሰሳሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኪቲም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፥ አሦርንም ያሠቃያሉ፥ ዔቦርንም ያስጨንቃሉ፤ እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወራሪዎች በመርከብ ከቆጵሮስ ይመጣሉ፤ እነርሱም አሦርንና ዔቤርን ያጠፋሉ፤ እነርሱም ራሳቸው ለዘለዓለም ይጠፋሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኪቲም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፥ አሦርንም ያስጨንቃሉ፥ ዔቦርንም ያስጨንቃሉ፤ እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት ይመጣል። |
ከአመለጡትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፤ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊው የመምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይቀጣል።
ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና።
ከባሳን ኮምቦል መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፤ መቅደስሽንም በዝኆን ጥርስ ሠሩ፤ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍም ቤቶችሽን ሠርተዋል።
አግንም ባየው ጊዜ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ አወይ ማን በሕይወት ይኖራል?