እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ታደርጋለህ” አለው።
ዘኍል 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለበለዓም ታየው፤ በለዓምም ለእግዚአብሔር፥ “እነሆ፥ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ተገናኘው፤ በለዓምም፣ “እነሆ፤ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጅቻለሁ፤ በእያንዳንዱም ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ አቅርቤአለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጣ፤ እርሱም፦ “ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ተገናኘው፤ በለዓምም “ሰባቱን መሠዊያዎች ሠርቼ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ የበግ አውራ አቅርቤአለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከበለዓም ጋር ተገናኘ፤ እርሱም፦ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ አለው። |
እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ታደርጋለህ” አለው።
በለዓምም ባላቅን፥ “በመሥዋዕትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔ እግዚአብሔር ቢገለጥልኝ፥ ቢገናኘኝም እሄዳለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ቃል እነግርሃለሁ” አለው። ባላቅም በመሠዊያው ዘንድ ቆመ፤ በለዓም ግን እግዚአብሔርን ይጠይቅ ዘንድ አቅንቶ ሄደ።
ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።