Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 23:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ለ​ዓም አፍ ቃልን አኖረ፤ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔርም በበለዓም አፍ መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመልሰህ ይህን መልእክት ንገረው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታም ቃልን በበለዓም አፍ አድርጎ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም ተናገር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔርም በለዓም ለባላቅ መናገር የሚገባውን መልእክት ከሰጠው በኋላ ወደዚያ ተመልሶ እንዲሄድ ነገረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም ቃልን በበለዓም አፍ አድርጎ፦ ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 23:5
14 Referencias Cruzadas  

አን​ተም ትና​ገ​ረ​ዋ​ለህ፤ ቃሌ​ንም በአፉ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔ አን​ደ​በ​ት​ህ​ንና አን​ደ​በ​ቱን አረ​ታ​ለሁ፤ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም አለ​ብ​ማ​ች​ኋ​ለሁ።


እግዚአብሔርን መፍራት በጎ ዕውቀትና ጥበብ ነው። ለሚመልስላትም የክብር መጀመሪያ ናት፥ የዋሃንንም ክብር ትከተላቸዋለች።


ኃጥእ ለክፉ ቀን ይጠበቃል።


ቃሌን በአ​ፍሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ሰማ​ይን በዘ​ረ​ጋ​ሁ​በ​ትና ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ት​ሁ​በት በእጄ ጥላ እጋ​ር​ድ​ሻ​ለሁ፤ ጽዮ​ን​ንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላ​ታ​ለሁ።


“ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጁን ዘር​ግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአ​ፍህ ውስጥ አኑ​ሬ​አ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም በሌ​ሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠ​ሩህ ዘንድ መጥ​ተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን ተገ​ና​ኘው፤ ቃል​ንም በአፉ አኖረ፥ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በለው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለበ​ለ​ዓም ታየው፤ በለ​ዓ​ምም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እነሆ፥ ሰባት መሠ​ዊ​ያ​ዎች አዘ​ጋ​ጀሁ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረ​ግሁ” አለው።


ወደ እር​ሱም ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ እር​ሱና የሞ​ዓብ አለ​ቆች ሁሉ በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ወደ እርሱ መጣ፤


ያን​ጊዜ በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ና​ገ​ረው መን​ፈስ ቅዱስ ነውና።”


ይህ​ንም ከልቡ የተ​ና​ገ​ረው አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዚ​ያች ዓመት የካ​ህ​ናት አለቃ ነበ​ርና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ስለ ሕዝብ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ይሞት ዘንድ ስላ​ለው ይህን ትን​ቢት ተና​ገረ።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቃሌ​ንም በአፉ አኖ​ራ​ለሁ፤ እንደ አዘ​ዝ​ሁ​ትም ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos