Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 23:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር ተገናኘው፤ በለዓምም፣ “እነሆ፤ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጅቻለሁ፤ በእያንዳንዱም ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ አቅርቤአለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጣ፤ እርሱም፦ “ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔርም ተገናኘው፤ በለዓምም “ሰባቱን መሠዊያዎች ሠርቼ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ የበግ አውራ አቅርቤአለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለበ​ለ​ዓም ታየው፤ በለ​ዓ​ምም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እነሆ፥ ሰባት መሠ​ዊ​ያ​ዎች አዘ​ጋ​ጀሁ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረ​ግሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም ከበለዓም ጋር ተገናኘ፤ እርሱም፦ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 23:4
12 Referencias Cruzadas  

በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጥቶ፣ “እነዚህ ሰዎች የመጡት እንድትሄድላቸው እስከ ሆነ ድረስ ዐብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ።”


እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፣ “ከአንተ ጋራ ያሉት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው።


በለዓም፣ “እዚህ ሰባት መሠዊያ ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት አውራ በጎችም አዘጋጅልኝ” አለው።


እግዚአብሔር በለዓምን ተገናኘው፤ በአፉም መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና ይህን መልእክት ንገረው” አለው።


ከዚያም በለዓም ባላቅን፣ “እኔ ወደዚያ ስሄድ፣ አንተ እዚሁ መሥዋዕትህ አጠገብ ቈይ፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ሊገናኘኝ ይመጣ ይሆናል፤ የሚገልጥልኝንም ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው። ከዚያም በለዓም ወደ አንድ ገላጣ ኰረብታ ሄደ።


እግዚአብሔርም በበለዓም አፍ መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመልሰህ ይህን መልእክት ንገረው” አለው።


‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት አንድ ሰዓት ብቻ ሲሠሩ፣ ቀኑን ሙሉ በሥራ ስንደክምና በፀሓይ ስንንቃቃ ከዋልነው ጋራ እንዴት እኩል ትከፍለናለህ?’ አሉት።


በሳምንት ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፤ ከማገኘውም ሁሉ ዐሥራት አወጣለሁ።’


ከምኵራብ ያስወጧችኋል፤ እንዲያውም የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንዳገለገለ የሚቈጥርበት ጊዜ ይመጣል።


ታዲያ ትምክሕት ወዴት ነው? እርሱማ ቀርቷል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ።


ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos