የእግዚአብሔርም ሰው ንጉሡን፥ “የቤትህን እኩሌታ እንኳን ብትሰጠኝ ከአንተ ጋር አልገባም፤ በዚህም ስፍራ እንጀራን አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም፤
ዘኍል 22:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለዓምም መልሶ የባላቅን አለቆች፥ “ባላቅ በቤቱ የሞላውን ወርቅና ብር ቢሰጠኝ፥ በትንሹ ወይም በትልቁ ቢሆን የአምላኬን የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓም ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጣስ ከዚያ ያለፈ ወይም ያነሰ ማንኛውንም ነገር ማድረግ አልችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም መልሶ የባላቅን ባርያዎች እንዲህ አላቸው፦ “ባላቅ በቤቱ የሞላውን ወርቅና ብር ቢሰጠኝ፥ ትንሹን ወይም ትልቁን ነገር በመፈጸም የአምላኬን የጌታን ቃል ለመተላለፍ አልችልም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓም ግን ለመልእክተኞቹ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “ባላቅ በቤተ መንግሥቱ የሚገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝም በትንሽ ወይም በትልቅ ነገር የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መተላለፍ አይቻለኝም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በለዓምም መልሶ የባላቅን ባሪያዎች፦ ባላቅ በቤቱ የሞላውን ወርቅና ብር ቢሰጠኝ፥ በትንሹ ወይም በትልቁ ቢሆን የአምላኬን የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤ |
የእግዚአብሔርም ሰው ንጉሡን፥ “የቤትህን እኩሌታ እንኳን ብትሰጠኝ ከአንተ ጋር አልገባም፤ በዚህም ስፍራ እንጀራን አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም፤
በለዓምም ባላቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያደርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ” አለው።
እርሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግዚእብሔርም የሚነግረኝን እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ የሞዓብ አለቆችም በበለዓም ዘንድ አደሩ።
ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ መልካሙን ወይም ክፉውን ከልቤ ለማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤ እግዚአብሔር የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞችህ አልተናገርኋቸውምን?