አንተም በትርህን አንሣ፤ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ዘኍል 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔር እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የነበረችውን በትሩን ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ሙሴ ልክ እንደ ታዘዘው በትሩን ከእግዚአብሔር ፊት ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንደ ታዘዘ በትሩን ከጌታ ፊት ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከድንኳኑ ውስጥ በትሩን አመጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንደ ታዘዘ በትሩን ከእግዚአብሔር ፊት ወሰደ። |
አንተም በትርህን አንሣ፤ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ሙሴም ሚስቱንና ልጆቹን ወሰደ፤ በአህዮች ላይም አስቀመጣቸው፤ ወደ ግብፅም ሀገር ተመለሰ፤ ሙሴም ያችን የእግዚአብሔርን በትር በእጁ ይዞ ሄደ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ፥ እነርሱም እንዳይሞቱ ለማይሰሙ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ ዘንድ የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አኑር።”