አሁንም እነሆ፥ እስራኤል ከግብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያልፉባቸው ዘንድ ያልፈቀድህላቸው የአሞንና የሞዓብ ልጆች፥ የሴይርም ተራራ ሰዎች እንዳያጠፉአቸው ከእነርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።
ዘኍል 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፤ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጎዳና እንሄዳለን፤ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፥ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጉድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ግዛትህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በምድርህ አልፈን እንድንሄድ እባክህ ፍቀድልን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን ከመንገድ ውጪ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም አንጠጣም፤ ግዛትህን እስክናልፍ ድረስ ከዋናው መንገድ አንወጣም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም። |
አሁንም እነሆ፥ እስራኤል ከግብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያልፉባቸው ዘንድ ያልፈቀድህላቸው የአሞንና የሞዓብ ልጆች፥ የሴይርም ተራራ ሰዎች እንዳያጠፉአቸው ከእነርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።
በአዜብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የአራድ ንጉሥ በአታሪን መንገድ እስራኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ሰልፍ አደረገ ከእነርሱም ምርኮ ማረከ።
በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች፥ በአሮዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በእግሬ ልለፍ።