ዘኍል 2:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በየዓላማዎቻቸው ሰፈሩ፤ እንዲሁም በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች እየሆኑ ተጓዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ፤ እያንዳንዱ ነገድ ዓርማውን በመከተል ይሰፍር ነበር፤ እያንዳንዱም በየቤተሰቡ ተመድቦ ይጓዝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ። |
“የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየሥርዐቱ፥ በየዓላማው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ አንጻር ይስፈሩ።
በያዕቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእስራኤልም ሕማም አይታይም፤ አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው፤ የአለቆችም ክብር ለእርሱ ነው።