ዘኍል 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየሥርዐቱ፥ በየዓላማው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ አንጻር ይስፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤላውያን ከምስክሩ ድንኳን ትይዩ ዙሪያውን ጥቂት ራቅ ብለው እያንዳንዱ ሰው በየዐርማውና በየቤተ ሰቡ ምልክት ሥር ይስፈር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን ትይዩ በሁሉም አቅጣጫ ይስፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በየተመደቡበት ቡድን ሰንደቅ ዓላማና በየነገዳቸው ዐርማ ሥር ይሰፍራሉ፤ አሰፋፈራቸውም የመገናኛው ድንኳን በዙሪያው ሆኖ ፊታቸው ከድንኳኑ ትይዩ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ፤ በመገናኛው ድንኳን አፋዛዥ ዙሪያ ይስፈሩ። |
እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው። ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው በአለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።
በዚያም ቀን አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፣ እነርሱም ለአክሊል እንደሚሆኑ እንደ ከበሩ ድንጋዮች ይሆናሉ፥ በምድሩም ላይ ይብለጨለጫሉ።
ነገር ግን በምስክሩ ድንኳንና በዕቃዎችዋ ሁሉ፥ በውስጥዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ድንኳንዋንና ዕቃዎችዋን ሁሉ ይሸከሙ፤ ያገልግሉአትም፤ በድንኳንዋም ዙሪያ ይስፈሩ።
በመጀመሪያም የይሁዳ ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን አለቃ ነበረ።
የኤፍሬምም ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የኣሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ አለቃ ነበረ።
ከሠራዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊታቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዲ ልጅ አኪያዜር አለቃ ነበረ።
በመጀመሪያ በምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት ከሠራዊቶቻቸው ጋር የይሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።
ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚኖርበት፥ በሥርና በጅማትም በሚስማማበት፥ በእግዚአብሔርም በሚያድግበትና በሚጸናበት፥ በሚሞላበትም በራስ አይጸናም።
በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት በስፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መንገድ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ።”