ዘኍል 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ድንኳን የሚነካ ሁሉ ይሞታል። በውኑ ሁላችን ፈጽመን እንሞታለን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚጠጋ እንኳ ማንኛውም ሰው ቢሆን ይሞታል፤ ሁላችንም ልንጠፋ ነው እንዴ?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጽሞ ወደ ጌታ ማደሪያ የሚቀርብ ሁሉ፥ ይሞታል፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለንን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ድንኳኑ የሚቀርብ ሁሉ የሚሞት ከሆነ ሁላችንም እንጠፋለን ማለት ነውን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቀርብ ሁሉ፥ ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚቀርብ፥ ይሞታል፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለንን? ብለው ተናገሩት። |
በዚያም ዳዊት ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረበ። ሰሎሞንም በኋላ ዘመን በመሠዊያው ላይ ጨመረ፤ ያንጊዜ አነስተኛ ነበርና። እግዚአብሔርም ስለ ሀገሪቱ የተለመነውን ሰማ፤ መቅሠፍቱም ከእስራኤል ተከለከለ።
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ።
ማኅበሩንም፥ “ከእነዚህ ክፉዎች ሰዎች ድንኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ ለእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ” ብሎ ተናገራቸው።
እግዚአብሔርም አሮንን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ወገኖች፥ የክህነታችሁን ኀጢአት ትሸከማላችሁ።
ያንም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ። ሁለቱንም እስራኤላዊውን ሰውና ምድያማዊቱን ሴት ሆዳቸውን ወጋቸው፤ ከእስራኤልም ልጆች መቅሠፍቱ ተወገደ።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ያደረገ ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ውስጥ አንከራተታቸው።