እናንተም፦ አይደለም፤ ሰልፍ ወደማናይባት፥ የመለከትም ድምፅ ወደማንሰማባት፥ እንጀራንም ወደማንራብባት ወደ ግብፅ ምድር እንሄዳለን፤ በዚያም እንቀመጣለን ብትሉ፥
ዘኍል 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ” ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸውም፣ “አለቃ መርጠን ወደ ግብጽ እንመለስ” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርስ በርሳቸውም፦ “ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብጽ እንመለስ” ተባባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እርስ በርሳቸው “ኑ! መሪ የሚሆነን ሰው መርጠን ወደ ግብጽ እንመለስ!” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳቸውም፦ ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ ተባባሉ። |
እናንተም፦ አይደለም፤ ሰልፍ ወደማናይባት፥ የመለከትም ድምፅ ወደማንሰማባት፥ እንጀራንም ወደማንራብባት ወደ ግብፅ ምድር እንሄዳለን፤ በዚያም እንቀመጣለን ብትሉ፥
ነገር ግን በመካከላችሁ ያለውን እግዚአብሔርን ንቃችኋልና፥ በፊቱም፦ ለምን ከግብፅ አወጣኸን? ብላችሁ አልቅሳችኋልና በአፍንጫችሁ እስኪወጣ መርዝም እስኪሆንባችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበሉታላችሁ።”
ለእርሱ ፈረሶችን እንዳያበዛ፥ ሕዝቡንም ወደ ግብፅ እንዳይመልስ፤ እግዚአብሔር፦ በዚያች መንገድ መመለስን አትድገም ብሎአልና።
ከእንግዲህ ወዲህ ተመልሰህ አታያትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልስሃል፤ በዚያም ለጠላቶቻችሁ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ የሚራራላችሁም አይኖርም።”