ዘኍል 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ ሕያው ነኝ፤ ስትናገሩ የሰማኋችሁን እነዚያን ነገሮች አደርግባችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ! ይህን መልስ ስጣቸው፥ ‘በጠየቃችሁት ዐይነት እንደማደርግባችሁ ሕያው በሆነ ስሜ እምላለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ |
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ይፈጸማል፤ ደግሞም አይዘገይም፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ! በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ፤ እፈጽመውማለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሕዝቡም በክፋት በእግዚአብሔር ፊት አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእነርሱ ላይ ነደደች፤ ከሰፈሩም አንዱን ወገን በላች።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከምንሞት በግብፅ ምድር ሳለን ብንሞት በተሻለን ነበር።
በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መልካምንና ክፉን ለይተው ለማያውቁ ልጆቻቸው፥ የሚያውቀው ለሌለ ለታናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰጣታለሁ፤ ለጥፋት ያነሳሱኝ ሁሉ አያዩአትም።
ከግብፅ የወጡት ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት መልካምንና ክፉን የሚያውቁ ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጥ ዘንድ የማልሁባትን ምድር አያዩም፤
የዛሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለባቸው ተዋጊዎች የሆኑ የዚያች ትውልድ ሰዎች ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።