የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።
ነህምያ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ ገዛ ከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። |
የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።
ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በጥሩ ድንጋይ ይሠራል፤ በቅጥሩም ውስጥ ልዩ እንጨት ይደረጋል፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል።
በሜዶን አውራጃ ባለው ባሪ በሚባል ከተማ በንጉሡ ቤት ውስጥ አንድ ጥቅልል ተገኘ፤ በውስጡም ይህ ነገር ለመታሰቢያ ተጽፎ ነበር።
እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከሄሜኔስ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበልሰማ፥ ከሚስፌሬት፥ ከዕዝራ፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና፥ ከመስፈር ጋር መጡ። ከእስራኤልም ሕዝብ የወንዶች ቍጥር ይህ ነው፥