የአይሁድ ሽማግሌዎችና ሌዋውያንም በነቢዩ በሐጌና በአዶ ልጅ በዘካርያስ ትንቢት መሠረት ሠሩ፤ ተከናወነላቸውም። እንደ እስራኤልም አምላክ ትእዛዝ፥ እንደ ፋርስም ነገሥታት እንደ ቂሮስና እንደ ዳርዮስ፥ እንደ አርተሰስታም ትእዛዝ ሠርተው ፈጸሙ።
ነህምያ 6:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅጥሩም በኤሉል ወር በሃያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅጥሩም ኤሉል በተባለው ወር ሃያ ዐምስተኛ ቀን፣ በዐምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጠናቀቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጠናቀቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥራው ከተጀመረ ከኀምሳ ሁለት ቀኖች በኋላ ኤሉል ተብሎ የሚጠራው ወር በገባ በሃያ አምስተኛው ቀን የቅጽሩ ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ። |
የአይሁድ ሽማግሌዎችና ሌዋውያንም በነቢዩ በሐጌና በአዶ ልጅ በዘካርያስ ትንቢት መሠረት ሠሩ፤ ተከናወነላቸውም። እንደ እስራኤልም አምላክ ትእዛዝ፥ እንደ ፋርስም ነገሥታት እንደ ቂሮስና እንደ ዳርዮስ፥ እንደ አርተሰስታም ትእዛዝ ሠርተው ፈጸሙ።
እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና።