አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ሥራቸው ጦቢያንና ሰንባላጥን፥ ነቢይቱንም ኖዓድያን ያስፈራሩኝ ዘንድ የፈለጉትን፥ የቀሩትንም ነቢያት አስብ።
ነህምያ 13:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላኬ ሆይ፥ ክህነትን የክህነትንና የሌዋውያንንም ቃል ኪዳን ስላፈረሱ አስባቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኬ ሆይ፤ የክህነትን ማዕርግ፣ የክህነትንና የሌዋውያንን ቃል ኪዳን ስላረከሱ ዐስባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላኬ ሆይ፥ ክህነትን የክህነትንና የሌዋውያንንም ቃል ኪዳን ስላፈረሱ አስባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፥ ይህ ሕዝብ ክህነትን፥ የክህነትን ሥርዓትንና አንተ ከካህናትና ከሌዋውያን ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን እንዴት እንዳረከሰ ተመልከት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላኬ ሆይ፥ ክህነትን የክህነትንና የሌዋውያንንም ቃል ኪዳን ስላፈረሱ አስባቸው። |
አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ሥራቸው ጦቢያንና ሰንባላጥን፥ ነቢይቱንም ኖዓድያን ያስፈራሩኝ ዘንድ የፈለጉትን፥ የቀሩትንም ነቢያት አስብ።
ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶችን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፤ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
የአምላክህን መባ ያቀርባልና ስለዚህ ትቀድሰዋለህ፤ እኔም የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና እርሱ ቅዱስ ይሁንልህ።
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት፤ ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።