ነህምያ 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበረ፤ የሰኑዋም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእነዚህም አለቃ የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ሲሆን፣ የሐስኑአ ልጅ ይሁዳ የከተማዪቱ ሁለተኛ አውራጃ የበላይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቃቸውም የዚክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበር፤ የሃስኑአ ልጅ ይሁዳ ደግሞ በከተማው ላይ ሁለተኛ የተሾመ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚክሪ ልጅ ኢዩኤል መሪያቸው ሲሆን፥ የሀስኑአ ልጅ ይሁዳ በማዕርግ ሁለተኛ የሆነ የከተማይቱ ባለሥልጣን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበር፥ የሐስኑአም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ። |
በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የመታንያ ልጅ፥ የሐሳብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።