ነህምያ 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ዘሮች በጠቅላላ 468 ብርቱ ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ኃያላን ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፋሬስ ዘሮች መካከል በጀግንነታቸው ታዋቂዎች የሆኑ 468 ሰዎች በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ። |
የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የይሳዕያ ልጅ፥ የአትያል ልጅ፥ የመዕሤያ ልጅ፥ የቆላያ ልጅ፥ የፈዳያ ልጅ፥ የዮሐድ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ ሴሎ።