ነህምያ 11:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም ላይ የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ፤ የመዘምራኑም ሥርዐት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዘምራኑ የየዕለቱን ተግባራቸውን በሚቈጣጠረው በንጉሡ ትእዛዝ ሥር ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እነርሱ የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ የመዘምራኑም ሥርዓት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየዕለቱ የሚቀርበውንም መዝሙር ቅደም ተከተል ተራ በማስያዝ ረገድ ከንጉሡ የተሰጠ ትእዛዝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እነርሱም የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ፥ የመዘምራኑም ሥርዓት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ። |
ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን በየሰሞናቸው አገልጋዮችና ሹሞች ነበሩ፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረ።
እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፤ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።