ናሆም 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር መልካም ነው፤ በጭንቅ ጊዜም መሸሸጊያ ነው። ለሚታመኑበት ይጠነቀቅላቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚሸሸጉትን ያውቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ቸር ነው፤ በመከራ ጊዜም ጠንካራ መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚተማመኑትን ሁሉ ይንከባከባል። |
በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና በእርሱም ታምነዋልና አዳናቸው፤ በላያቸውም በረቱባቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።
በዚያም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ የይሁዳም ልጆች በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ነበርና አሸነፉ።
አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል እያለ ለራብ፥ ለጥምና ለሞት አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ የሚያሳስታችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን?
እግዚአብሔርም መልአኩን ላከ፤ እርሱም ጽኑዓን ኀያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።
ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳን የሚዋጋልንም አምላካችን እግዚአብሔር ነው።” ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና።
ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት በተመሠረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩ በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።
ባልንጀራውን በስውር የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፤ በዐይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም።
ለተዋረዱ ሰዎች ከተሞች ረዳት ሆነሃልና፥ በችግራቸው የተጨነቁትን በደስታ ጋረድሃቸው፤ ከክፉዎች ሰዎችም አዳንሃቸው፤ ለተጠሙት ጥላ ሆንሃቸው፤ ለተገፉትም ሕይወት ሆንሃቸው።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለበጎነት እመለከተዋለሁ።
የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የዚያችን ምድር ምርኮኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ይራራል፤ የእስራኤልንም ልጆች ያጸናል።
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ርኅራኄውንና ጭካኔውን አስተውል፤ የወደቁትን ቀጣቸው፤ አንተን ግን ይቅር እንዳለህ ብትኖር ማረህ፤ ያለዚያ ግን አንተም ትቈረጣለህ።
ዛሬ ግን እግዚአብሔርን ዐወቃችሁት፤ ይልቁንም እርሱ ዐወቃችሁ፤ እንደ ገና ደግሞ ወደዚያ ወደ ደካማው፥ ወደ ድሀው ወደዚህ ዓለም ጣዖት ተመልሳችሁ፥ ትገዙላቸው ዘንድ እንዴት ፈጠራን ትሻላችሁ?
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።