ሚክያስ 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜከላ፣ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኵርንችት ነው፤ የጠባቂዎቻችሁ ቀን ደርሷል፤ የአምላክ የፍርድ ቀን መጥቷል፤ የሚሸበሩበትም ጊዜ አሁን ደርሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ መካከል እጅግ የተሻለ ነው የተባለው ሰው እንደ አሜከላ ነው፤ እጅግ ትክክለኛ ነው የተባለው እንደ ኲርንችት ነው፤ በነቢያቱ አማካይነት ባስጠነቀቃቸው መሠረት እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚቀጣበት ጊዜ ይመጣል፤ እነሆ አሁንም ቢሆን በሽብር ላይ ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ። |
ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሁከትና የጥፋት፥ የመረገጥና የስብራትም ቀን በጽዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል። ታናሹና ታላቁም ሸሽተው በተራራ ላይ ይቅበዘበዛሉ።
በእሾህም ፋንታ ጥድ፥ በኵርንችትም ፋንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ የእግዚአብሔርም ስም ለዘለዓለም በማይጠፋ ምልክት ይመሰገናል።
በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች በእርስዋ ተቀልበው እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፤ በአንድነትም ሸሹ፤ አልቆሙምም።
አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤ ይላል እግዚአብሔር።
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ከአሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቈስል ኩርንችት አይሆንም፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
እርሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው” አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አልላቸውም።
“በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ይጨነቃሉ፤ ከባሕሩና ከሞገዱ ድምፅ የተነሣም ይሸበራሉ።