ሚክያስ 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሪሳ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፥ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዶላም ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በመሪሳ የምትኖሩ ድል አድራጊ አመጣባችኋለሁ፤ ያ የእስራኤል ክብር የሆነው ወደ ዓዶላም ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማሬሻ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፤ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዱላም ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመሪሳ ሕዝብ ሆይ! ወራሪ ጠላት አመጣባችኋለሁ፤ የተከበሩ የእስራኤል መሪዎችም በዐዱላም ዋሻ ይሸሸጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመሪሳ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፥ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዶላም ይመጣል። |
ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ወደ ቃሶን ወደ ዳዊት ወደ አዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
ስለ አሞን ልጆች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሚልኮም ጋድን ይወርስ ዘንድ ሕዝቡም በከተሞቹ ላይ ይቀመጥ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን?
ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ አመለጠ፤ ወደ ዔዶላም ዋሻም መጣ፤ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደዚያ ወረዱ።