በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው።
ማቴዎስ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ ቅድስት ከተማ በመውሰድ ከቤተ መቅደሱም ዐናት ላይ አውጥቶ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወስዶ በቤተ በመቅደሱ ጫፍ ላይ አቆመውና አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ፥ ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ ቅድስት ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደስ ጣራ ጫፍ ላይ አቆመው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦ |
በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው።
የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከዐሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ።
በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፥ ይህን ስሙ።
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይልሽን ልበሺ፤ አንቺም ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያልፍምና ክብርሽን ልበሺ።
ወደ ኢየሩሳሌምም ወስዶ በቤተ መቅደሱ የማዕዘን ጫፍ ላይ አቆመው፤ እንዲህም አለው፥ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህስ አንተ ራስህ ወደ ታች መር ብለህ ውረድ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህም፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢኣት አለበት” አለው።