“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔርም እንደምቀና ታያለህ” አለው። ከእርሱም ጋር በሰረገላው አስቀመጠው።
ማቴዎስ 23:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለመታየት ሲሉ የሚያደርጉትን ሁሉ በሰው ፊት ያደርጋሉ፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የቀሚሳቸውን ዘርፍ ያስረዝማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት ሰው እንዲያይላቸው ነው፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት ሰው እንዲያይላቸው ብለው ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የጸሎት ልብሳቸውን ዘርፍ ያስረዝማሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥ |
“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔርም እንደምቀና ታያለህ” አለው። ከእርሱም ጋር በሰረገላው አስቀመጠው።
እግዚአብሔርም በበረታች እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና የእግዚአብሔር ሕግ በአፍህ ይሆን ዘንድ በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ።
ካህኑም በሰባተኛው ቀን ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ ባይሰፋ፥ በውስጡም ብጫ ጠጕር ባይኖር፥ የቈረቈሩም መልክ ወደ ቆዳው ባይጠልቅ፤ ይላጫል፤
እርሱም፥ “እናንተስ ለሰው ይምሰል ትመጻደቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ልቡናችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ይሆናልና።
ከባልንጀራችሁ ክብርን የምትመርጡ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም ክብርን የማትሹ እናንተ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?
“እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፤ በዐይኖቻችሁም መካከል እንደማይንቀሳቀስ ይሁኑ።
ከእነርሱ አንዳንዶች በቅናታቸውና በክርክራቸው፥ ሌሎችም በበጎ ፈቃድ ስለ ክርስቶስ ሊሰብኩና ሊያስተምሩ የወደዱ አሉ።
በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ።
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።