La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 22:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢየሱስም እንዲህ አለው “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።’

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም እንዲህ አለው፤ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም እንዲህ አለው “‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፥ በሙሉ ነፍስህ፥ በሙሉ ሐሳብህ ውደድ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 22:37
13 Referencias Cruzadas  

“መምህር ሆይ! ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት?” ብሎ ጠየቀው።


ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።


በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።


እር​ሱም መልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ትህ፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልህ፥ በፍ​ጹም ዐሳ​ብህ ውደ​ደው፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው።


የሥጋ ዐሳብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ስለ​ማ​ይ​ገዛ፥ መፈ​ጸም አይ​ቻ​ለ​ውም።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አሁ​ንስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈራ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ታመ​ል​ከው ዘንድ ነው እንጂ፥


በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖር፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ እን​ድ​ት​ወ​ድድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም ልብ ያጠ​ራ​ዋል።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ፥ በፍ​ጹ​ምም ኀይ​ልህ ውደድ።


እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።