ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ማቴዎስ 18:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩም ያለበትን ዕዳ መክፈል ስላቃተው እርሱ ራሱ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹና ንብረቱ ሁሉ ተሸጠው ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መክፈልም ሲያቅተው እርሱ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ያለውም ሁሉ ተሽጠው ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ አገልጋይ ዕዳውን መክፈል ስላልቻለ እርሱም፥ ሚስቱም፥ ልጆቹም፥ ያለውም ንብረት ሁሉ ተሸጦ ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። |
ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
አሁንም ሥጋችን እንደ ወንድሞቻችን ሥጋ፥ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ እነሆም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ባሪያዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥተናል፤ ከሴቶችም ልጆቻችን ባሪያዎች ሆነው የሚኖሩ አሉ፤ ታላላቆችም እርሻችንንና ወይናችንን ይዘዋልና ልናድናቸው አንችልም” የሚሉ ነበሩ።
እኔም፥ “ለአሕዛብ የተሸጡትን ወንድሞቻችንን አይሁድን በፈቃዳችን ተቤዠን፤ እናንተስ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁን? እነርሱስ ለእኛ የተሸጡ ይሆናሉን?” አልኋቸው። እነርሱም ዝም አሉ፤ መልስም አላገኙም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።