ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤልያብ ልጅ የኬጤያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለው።
ማቴዎስ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤ |
ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤልያብ ልጅ የኬጤያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለው።
የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ የቀባው፥ የታማኙ ሰው፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የታማኙ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር ይህ ነው፤
ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።
እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
ስለ ሥጋ ደካማነት የኦሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተሳነው ጊዜ እግዚአብሔር በኀጢኣተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያችንም ኀጢአት በሥጋው ቀጣት።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።
ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፤ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፤ ስምንት ልጆችም ነበሩት፤ እሴይም በሳኦል ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።
ሁላችሁ በላዬ ዶልታችሁ ተነሣችሁብኝ፤ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ሲማማል ማንም አልገለጠልኝም፤ ከእናንተም አንድ ለእኔ የሚያዝን የለም፤ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ አገልጋዬን እንዲዶልት ሲያስነሣብኝ ማንም አላስታወቀኝም” አላቸው።