ማርቆስ 13:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ትጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። |
እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወንድሜ ቃል ደጅ እየመታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።
ሁሉም ዕውራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ በመኝታቸውም ሕልምን ያልማሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።