እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣቸዋል፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳቸዋል፤
ማርቆስ 10:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። ዕውሩንም “አይዞህ፤ ተነሣ፤ ይጠራሃል፤” ብለው ጠሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ቆም ብሎ፣ “ጥሩት” አላቸው። እነርሱም ዐይነ ስውሩን፣ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ቆም ብሎ፥ “ጥሩት” አላቸው። እነርሱም ዐይነ ስውሩን፥ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት!” አለ፤ እነርሱም ዕውሩንም “በል በርታ! ተነሥ! ኢየሱስ ይጠራሃል!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ቆመና፦ ጥሩት አለ። ዕውሩንም፦ አይዞህ፥ ተነሣ፥ ይጠራሃል ብለው ጠሩት። |
እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣቸዋል፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳቸዋል፤
እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።
ስለዚህም የሕዝብን ኀጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።
ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው።