ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮአስ እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ ከመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ካህናቱ አልጠገኑትም ነበር።
ሚልክያስ 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳት እንዳታነድዱ፣ ምነው ከእናንተ አንዱ የቤተ መቅደሱን ደጅ በዘጋ ኖሮ! እኔ በእናንተ ደስ አይለኝም፤ ከእጃችሁም ምንም ዐይነት ቍርባን አልቀበልም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ መካከል በሮችን የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። ቁርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳትን ከምታቃጥሉበት ይልቅ የቤተ መቅደሱን በር የሚዘጋ ምነው ከእናንተ አንድ ሰው እንኳ በተገኘ! በእናንተ ደስ ስለማይለኝ ለእኔ የምታቀርቡትን ቊርባን አልቀበልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮአስ እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ ከመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ካህናቱ አልጠገኑትም ነበር።
እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፥ “መቅበዝበዝን ወድደዋል፤ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፤ በደላቸውንም አሁን ያስባል፤ ኀጢአታቸውንም ይጐበኛል።”
ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ቢያቀርቡም ደስ አልሰኝባቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ።”
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋልና፥ ከሐሳዊ ነቢይ ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ሐሰትን አደረጉ።
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
እናንተ፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፣ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፣ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።
ይህን ከሚያደርግ ሰው፥ እግዚአብሔር የሚጠራውንና የሚመልሰውን ለሠራዊትም ጌታ ለእግዚአብሔር ቍርባን የሚያቀርበውን ከያዕቆብ ድንኳን ያጠፋል።
ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል፣ እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኅዘንም ትከድናላችሁ።
ጠባቂ ያይደለ፥ በጎቹም ገንዘቡ ያይደሉ ምንደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም መጥቶ በጎችን ይነጥቃቸዋል፥ ይበትናቸዋልም።
የጣዖታቱ ካህናት የጣዖታቱን መባ እንደሚበሉ አታውቁምን? መሠዊያውን የሚያገለግሉም መሥዋዕቱን እንደሚካፈሉ አታውቁምን? ለቤተ እግዚአብሔር ሹሞች መተዳደሪያቸው የቤተ እግዚአብሔር መባ ነው።
በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤