የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ሉቃስ 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ዐውቀው ተከተሉት፤ እርሱም ተቀበላቸው፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም አስተማራቸው፤ ሊፈወሱ የሚሹትንም አዳናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ይህንኑ ዐውቀው ተከተሉት፤ እርሱም ተቀብሏቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር፤ ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ይህንን አውቀው ተከተሉት፤ ተቀብሎአቸውም ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር፤ ፈውስም ያስፈልጋቸው የነበሩትንም ፈወሳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም ኢየሱስ የት እንደ ሆነ ባወቁ ጊዜ ተከተሉት፤ እርሱም ተቀበላቸውና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተማራቸው፤ ከበሽታ መዳን ፈልገው የመጡትንም በሽተኞች ሁሉ ፈወሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም አውቀው ተከተሉት፤ ተቀብሎአቸውም ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር፥ መፈወስ ያስፈለጋቸውንም ፈወሳቸው። |
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው?” “ፊተኛው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ በየከተማዉና በየመንደሩ ተመላለሰ፤ የእግዚአብሔርንም መንግሥት ሰበከላቸው፤ አስተማራቸውም፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ከእርሱ ጋር ነበሩ።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ለእናንተ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነዚያ ግን አይተው እንዳያዩ፥ ሰምተውም እንዳይሰሙ፥ እንዳያስተውሉም በምሳሌ ነው።
ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት፤ እርሱም ለብቻቸው ይዞአቸው ቤተ ሳይዳ ከምትባል ከተማ አጠገብ ወደ አለ ምድረ በዳ ወጡ።
ቀኑም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፥ “ያለንበት ምድረ በዳ ነውና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩ የሚበሉትንም እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት” አሉት።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
ማንም ሳይከለክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ ነበር፤ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እጅግ ገልጦ ያስተምር ነበር።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።