Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን ያላ​መ​ኑ​በ​ትን እን​ዴት ይጠ​ሩ​ታል? ባል​ሰ​ሙ​ትስ እን​ዴት ያም​ናሉ? ያለ ሰባ​ኪስ እን​ዴት ይሰ​ማሉ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ስለ እርሱስ ሳይሰሙ እንዴት ያምኑበታል? ሰባኪ ሳይኖር እንዴት መስማት ይችላሉ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ያልሰሙትንስ እንዴት ያምኑታል? ያለ ሰባኪስ እንዴት ሊሰሙ ይችላሉ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነገር ግን ሳያምኑበት እንዴት ሊጠሩት ይችላሉ? ስለ እርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምናሉ? ያለ አስተማሪስ እንዴት ሊሰሙ ይችላሉ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 10:14
22 Referencias Cruzadas  

በዘመኑም ጊዜ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤


ያለ እም​ነ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ማሰ​ኘት አይ​ቻ​ልም፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርብ ሰው አስ​ቀ​ድሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳለ፥ ለሚ​ሹ​ትም ዋጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሊያ​ምን ይገ​ባ​ዋል።


ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “ያስ​ተ​ማ​ረኝ ሳይ​ኖር በምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ወጥቶ አብ​ሮት ይቀ​መጥ ዘንድ ፊል​ጶ​ስን ለመ​ነው።


የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል፤ ጌታም ያስነሣዋል፤ ኀጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።


በር​ግጥ ከሰ​ማ​ች​ሁት፥ እው​ነት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነውና እው​ነ​ትን በእ​ርሱ ዘንድ ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤


ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።


“ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በውኑ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አል​ተ​ቀ​በ​ል​ንም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳለ ስንኳ አል​ሰ​ማ​ንም” አሉት።


በስሙ እን​ዲ​ያ​ምኑ አሕ​ዛ​ብን ልና​ስ​ተ​ምር ሐዋ​ር​ያት ተብ​ለን የተ​ሾ​ም​ን​በ​ትና ጸጋን ያገ​ኘ​ን​በት፥


ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።


መር​ከ​በ​ኞ​ቹም ፈሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ አም​ላኩ ጮኸ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም እን​ድ​ት​ቀ​ል​ል​ላ​ቸው በው​ስ​ጥዋ የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መር​ከቡ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝ​ቶም ያን​ኳ​ርፍ ነበር።


ያ ሰውም፥ “አቤቱ፥ አም​ን​በት ዘንድ እርሱ ማነው?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን።


ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕ​ሩን ተሻ​ግሮ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን ነው? እን​ዳ​ትል ከባ​ሕሩ ማዶ አይ​ደ​ለ​ችም።


‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፤’ አሉት። እርሱም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ፤’ አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios