ሉቃስ 8:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አዳነችሽ፤ በሰላም ሂጂ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ልጄ ሆይ፤ እምነትሽ ፈውሶሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ!” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት። |
ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶርም ተመለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞች እሄዳለሁ” አለው። ዮቶርም ሙሴን፥ “በደኅና ሂድ” አለው።
እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።
ሴቲቱም እንዳልተሰወረላት ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ሄዳ ሰገደችለት፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት በምን ምክንያት ወደ እርሱ እንደ ቀረበችና የልብሱን ጫፍ እንደ ዳሰሰች ወዲያውም እንደ ዳነች ተናገረች።
እርሱም ጳውሎስን ሲያስተምር ሰማው፤ ጳውሎስም ትኩር ብሎ ተመለከተው፤ እምነት እንዳለውና እንደሚድንም ተረዳ።
ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛም የምሥራች ተሰብኮልናል፤ ነገር ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።