ሉቃስ 6:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕንጭህን ለሚመታህም ሁለተኛይቱን ስጠው፤ መጐናጸፊያህን ለሚወስድም ቀሚስህን ደግሞ አትከልክለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱን ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ ስጠው፤ መጐናጸፊያህን ለሚወስድብህ እጀ ጠባብህን አትከልክለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጉንጭህን ደግሞ ስጠው፤ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን እንኳ አትከልክለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱን ጒንጭህን በጥፊ ለሚመታህ፥ ሌላውንም ጒንጭህን እንዲመታ አዙርለት፤ ነጠላህን ለሚወስድብህ፥ እጀ ጠባብህንም ጨምረህ ስጠው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕንጭህን ለሚመታህ ደግሞ ሁለተኛውን ስጠው፥ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው። |
የካህናንም ልጅ ሴዴቅያስ ቀረበ፤ ሚክያስንም በጥፊ መታውና፥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ በምን መንገድ ከእኔ አለፈ?” አለው።
ይህንም ባለጊዜ ከቆሙት ሎሌዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልስለታለህን?” ብሎ ጌታችን ኢየሱስን በጥፊ መታው።
እኛ እስከዚች ቀን ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፤ እንራቈታለን፤ እንሰደዳለን፤ ማረፊያም የለንም፤ እንደበደባለንም።
እንግዲህ ፀብና ክርክር ካላችሁ፥ ከመጀመሪያው ጀምሮ ውርደት እንደሚሆንባችሁ ዕወቁ፤ እንግዲያማ እንዴት አትነጠቁም? እንዴትስ አትገፉም?
የሚገዙአችሁንና የሚቀሙአችሁን፥ መባያ የሚያደርጓችሁንና የሚታበዩባችሁን፥ ፊታችሁንም በጥፊ የሚመትዋችሁን ትታገሡአቸዋላችሁና።
በእስራቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመከራ ተባብራችኋል፤ የገንዘባችሁንም መዘረፍ በደስታ ተቀብላችኋል፤ በሰማያት ለዘለዓለም የሚኖር ከዚህ የሚበልጥና የተሻለ ገንዘብ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና።