ንጉሡም ኢዮርብዓም የእግዚአብሔርን ሰው፥ “አሁን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ” አለው፥ የእግዚአብሔርም ሰው እግዚአብሔርን ለመነ፤ የንጉሡም እጅ ወደ እርሱ ተመለሰች። እንደ ቀድሞም ሆነች።
ሉቃስ 6:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚረግሙአችሁን መርቁአቸው፤ ለሚበድሉአችሁም ጸልዩላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚበድሏችሁም ጸልዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚበድሉአችሁም ጸልዩላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። |
ንጉሡም ኢዮርብዓም የእግዚአብሔርን ሰው፥ “አሁን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ” አለው፥ የእግዚአብሔርም ሰው እግዚአብሔርን ለመነ፤ የንጉሡም እጅ ወደ እርሱ ተመለሰች። እንደ ቀድሞም ሆነች።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ፍልስጥኤማውያን በቀልን አድርገዋልና፥ በቀላቸውንም አጽንተዋልና፥ እስራኤልም ለዘለዓለም ይጠፉ ዘንድ ነፍሳቸው ደስ ይላታልና፤
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንአቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን ኣያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ፤ በልብሱም ላይ ዕጣ ተጣጣሉና ተካፈሉ።
አሁንም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉላቸው፤ እንዲመልሱላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ብዙ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለበጎዎችና ለክፉዎች ቸር ነውና።
በጕልበቱም ተንበርክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢአት አትቍጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ ሞተ፤ ሳውልም በእስጢፋኖስ ሞት ተባባሪ ነበር።
በእጃችን ሥራ እያገለገልን እንደክማለን፤ ይረግሙናል፤ እኛ ግን እንመርቃቸዋለን፤ ያሳድዱናል፤ እኛ ግን እንጸልይላቸዋለን፤ እንታገሣቸዋለንም።