Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አሕ​ዛ​ብና አይ​ሁድ ግን ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ሊያ​ን​ገ​ላ​ት​ዋ​ቸ​ውና በድ​ን​ጋይ ሊደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዚህ ጊዜ አሕዛብና አይሁድ ከመሪዎቻቸው ጋራ ተባብረው ሊያንገላቷቸውና በድንጋይ ሊያስወግሯቸው ሞከሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አሕዛብና አይሁድ ግን ከአለቆቻቸው ጋር ሊያንገላቱአቸውና ሊወግሩአቸው ባሰቡ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አሕዛብና አይሁድ ከአለቆቻቸው ጋር ሆነው ጳውሎስንና በርናባስን ሊያንገላቱአቸውና በድንጋይ ሊወግሩአቸው ፈለጉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አሕዛብና አይሁድ ግን ከአለቆቻቸው ጋር ሊያንገላቱአቸውና ሊወግሩአቸው ባሰቡ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 14:5
16 Referencias Cruzadas  

አይ​ሁ​ድም ከአ​ን​ጾ​ኪ​ያና ከኢ​ቆ​ንያ መጡ፤ ልባ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ጠ​ኑ​ባ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አባ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም እየ​ጐ​ተቱ ከከ​ተማ ውጭ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት፤ የሞ​ተም መሰ​ላ​ቸው።


ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።


የማ​ያ​ምኑ አይ​ሁድ ግን ቀኑ​ባ​ቸው፤ ከገ​በ​ያም ክፉ​ዎች ሰዎ​ችን አም​ጥ​ተው፥ ሰዎ​ች​ንም ሰብ​ስ​በው ሀገ​ሪ​ቱን አወ​ኳት፤ ፈለ​ጓ​ቸ​ውም፤ የኢ​ያ​ሶ​ንን ቤትም በረ​በሩ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ሊያ​ወ​ጧ​ቸው ሽተው ነበር።


የሚ​ረ​ግ​ሙ​አ​ች​ሁን መር​ቁ​አ​ቸው፤ ለሚ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁም ጸል​ዩ​ላ​ቸው።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


አቤቱ፥ ርዳ​ታው ከአ​ንተ ዘንድ የሆ​ነ​ለት፥ በል​ቡም የላ​ይ​ኛ​ውን መን​ገድ የሚ​ያ​ስብ ሰው ብፁዕ ነው።


አይ​ሁ​ድም የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውን ብዙ ሕዝብ ባዩ ጊዜ ቀኑ​ባ​ቸው፤ እየ​ተ​ሳ​ደ​ቡም ጳው​ሎስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ተቃ​ወሙ።


አይ​ሁድ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ የከ​በሩ ሴቶ​ች​ንና የከ​ተ​ማ​ውን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች አነ​ሳ​ሡ​አ​ቸው፤ በጳ​ው​ሎ​ስና በበ​ር​ና​ባስ ላይም ስደ​ትን አስ​ነሡ፤ ከሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው።


ማመ​ንን እንቢ ያሉት የአ​ይ​ሁድ ወገ​ኖች ግን የአ​ሕ​ዝ​ብን ልብ በወ​ን​ድ​ሞች ላይ አነ​ሣሡ፤ አስ​ከ​ፉም።


የከ​ተ​ማ​ውም ሕዝብ ሁሉ ተለ​ያዩ፤ እኩ​ሌ​ቶቹ ወደ አይ​ሁድ፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ወደ ሐዋ​ር​ያት ሆኑ።


በመ​ን​ገድ ዘወ​ትር መከራ እቀ​በል ነበር፤ በወ​ን​ዝም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ወን​በ​ዴ​ዎ​ችም አሠ​ቃ​ዩኝ፤ ዘመ​ዶ​ችም አስ​ጨ​ነ​ቁኝ፤ አሕ​ዛብ መከራ አጸ​ኑ​ብኝ፤ በከ​ተማ መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በበ​ረ​ሃም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ በባ​ሕ​ርም መከራ ተቀ​በ​ልሁ፤ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራን መከራ አጸ​ኑ​ብኝ።


ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።


እናንተ ወንድሞች ሆይ! በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና።


ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios