በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”
ሉቃስ 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንዲት ከተማ ሳለም ሁለመናው ለምጻም የሆነ ሰው መጣ፤ ጌታችን ኢየሱስንም ባየው ጊዜ በፊቱ ወድቆ ሰገደለትና፥ “አቤቱ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” እያለ ማለደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ከከተሞች በአንዱ በነበረበት ጊዜ፣ አንድ ለምጽ የወረሰው ሰው በዚያው ከተማ ነበር፤ ይህ ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ በፊቱ ተደፋና፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ብሎ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የወረሰው አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ፦ “ጌታ ሆይ! ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ተማጸነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ኢየሱስ በአንዲት ከተማ ውስጥ ሳለ ገላውን ለምጽ የወረሰው አንድ ሰው ወደ እርሱ መጣ፤ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ ጌታ ሆይ፥ “ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማዎችም በአንዲቱ ሳለ፥ እነሆ፥ ለምጽ የሞላበት ሰው ነበረ፤ ኢየሱስንም አይቶ በፊቱ ወደቀና፦ ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው። |
በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”
ሕዝቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው፥ “እግዚአብሔር በእውነት እርሱ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው” አሉ።
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።
ነገር ግን የንዕማን ለምጽ በአንተና በዘርህ ላይ፥ ለዘለዓለም ይመለስ” አለው። እንደ በረዶም ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትና ሽማግሌዎቹም ማቅ ለብሰው በግንባራቸው ተደፉ።
ዳግመኛም እግዚአብሔር፥ “እጅህን ወደ ብብትህ አግባ አለው።” እጁንም ወደ ብብቱ አገባት፤ “እጅህንም ከብብትህ አውጣ” አለው፤ እጁንም ከብብቱ አወጣ፤ እጁም ለምጽ ሆነች።
እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ።
ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ኢየሱስም “ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን?” አላቸው። “አዎን፥ ጌታ ሆይ!” አሉት።
“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋውያን ካህናት ያስተማሩህን ሁሉ ፈጽመህ እንድትጠብቅ እንድታደርግም ተጠንቀቅ፤ እኔ ያዘዝኋቸውን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።
ዘወትር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሊያድናቸው ይቻለዋል፤ ለዘለዓለምም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል።
እርሱም፥ “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፥ “በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል?” አለው።