Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ሰው​የ​ውም ሳም​ራዊ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በኢየሱስም እግር ላይ በፊቱ ተደፍቶ አመሰገነው፤ ይህም ሰው ሳምራዊ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ኢየሱስንም እያመሰገነ በእግሩ ሥር በግምባሩ ተደፋ፤ እርሱ የሰማርያ ሰው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 17:16
21 Referencias Cruzadas  

እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፤ አዘዛቸውም፤ እንዲህም አለ “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፤ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤


ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።


አራቱም እንስሶች ‘አሜን’ አሉ፤ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።


ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤” ክብር ውዳሴ ኃይልም እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።


ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ና​ንተ ላይ በወ​ረደ ጊዜ ኀይ​ልን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ሁሉ፥ በሰ​ማ​ር​ያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረ​ስም ምስ​ክ​ሮች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ።”


ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና።


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።


ሰዎች ሁሉ አብን እን​ደ​ሚ​ያ​ከ​ብሩ ወል​ድን ያከ​ብሩ ዘንድ፤ ወል​ድን የማ​ያ​ከ​ብር ግን የላ​ከ​ውን አብን አያ​ከ​ብ​ርም።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


ሴቲቱ ግን የተደረገላትን ስላወቀች፥ እየፈራች እየተንቀጠቀጠችም፥ መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ እውነቱንም ሁሉ ነገረችው።


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።


አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፤ “የነጹ ዐሥር አል​ነ​በ​ሩ​ምን? እን​ግ​ዲህ ዘጠኙ የት አሉ?


በል​ባ​ቸው የደ​በ​ቁ​ትም ይገ​ለ​ጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማ​ያ​ም​ነው ተመ​ልሶ ይጸ​ጸ​ታል፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳል፥ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳ​ለም ይና​ገ​ራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios